አጫጭር መረጃዎች
~ በታይዋን እና በአለም የጤና ድርጅት መካከል ያለዉ ዉዝግብ በዛሬዉ እለት ቀጥሎ ዉሏል፡፡የአለም የጤና ድርጅት የቃላት ጨዋታን መጫወት ቀጥሏል ስትል ታይዋን ተናግራለች፡፡ታይዋን የድርጅቱ አባል እንዳልሆነች የሚታወቅ ሲሆን ቻይና ታይዋንን ግዛቴ ናት ትላለች፡፡
~ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የሀሰት መረጃን ያሰራጩ ቢያንስ 226 ሰዎች በ10 የእስያ ሀገራ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ከሀገራቱ መካከል ህንድ፣ሞንጎሊያ፣ታይላንድ ይገኙበታል፡፡
~ በብራዚል ከ1ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ ማለፉ ተሰማ፡፡1‚056 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን ሲያጡ 20ሺ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡አሁንም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቦልሴናሮ ተገቢዉን ትኩረት ለቫይረሱ እየሰጡ ግን አይደለም፡፡ እንቅስቃሴን የሚከለክል ህግ እንዳይወጣ እየተከላከሉ ይገኛል፡፡
~ የእንግሊዝ የጤና ባለሙያዎች ያለ በቂ የመከላከያ ቁሳቁስ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ተነገረ፡፡ይህንን ተከትሎ የብሄራዊ የጤና አገልግሎቱ የእንግሊዝ መንግስትት በተደጋጋሚ መተቸቱን ቀጥሏል፡፡በእንግሊዝ በቫይረሱ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 8‚958 ደርሷል፡፡
~ በሩሲያ በ24 ሰዓት ዉስጥ ብቻ 1‚667 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተሰማ፡፡በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13‚584 ሲደርስ የ106 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፡፡የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ኮንቴ ለቀጣዮቹ 22 ቀናት እንቅስቃሴ የሚከለክለዉን ህግ አራዝመዋል፡፡በቀጣይ ሳምንታ አንዳንድ ሱቆች በጣሊያን እንደሚከፈቱ ይጠበቃል፡፡
~ ባንግላዲሽ እንቅስቃሴ የሚከለክለዉን ህግ ለ11 ቀናት ማራዘሟን አስታዉቃለች፡፡ህንድ በበኩሏ እንቅስቃሴ የሚከለክለዉን መመሪያ ብታራዝምም የጠቅላይ ሚንስትር ናሬድራ ሞዲ አስተዳደር እስከ መቼ የሚለዉን ይፋ አላደረገም፡፡
~ የጤና ባለሙያዎችና ፖለቲከኞች አሜሪካዉያን በነገዉ እለት የሚከበረዉን የትንሳዔ በዓል በማስመልከት ወደ ቤተክርስሪያን እንዳያቀኑ አስጠንቅቀዋል፡፡በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር 18‚761 ደርሷል፡፡