መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 3፣ 2012 ዓ.ም


በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሊጀመር ነው።
ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ እንደገለጹት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሁሉም ወረዳዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይጀመራል።
ምርመራው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ከተለዩ ወረዳዎች የሚጀምር መሆኑን ገልጸው በመዲናዋ 117ቱም ወረዳዎች ይከናወናል ብለዋል።
ለምርመራው ጡረታ ላይ የነበሩና በሞያው ልምድ ያላቸው ከ1 ሺህ 200 በላይ ሃኪሞች የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ካሉት ሃኪሞች ጋር ተጨማሪ ሃይል በመሆን ዝግጁ መሆናቸውንም ከንቲባው ገልጸዋል።
ምንጭ፦ኢዜአ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *