መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 6፣ 2012 ዓ.ም

አጫጭር መረጃዎች

~ ታይላንድ እና ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ የቃላት ጦርነት እየተደረገ ይገኛል፡፡የቲዉተር ጦርነት የተባለ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የዉሃን ቫይረስ ተብሎ መገለጹ ብሎም በቻይና ላብራቶሪ የተፈጠረ ቫይረስ መባሉ የዉዝግቡ አካል ሆኗል፡፡

~ በለንደን የሚገኘዉ ሂትሮ ኤርፖርት በወርሃ ሚያዚያ 90 በመቶ በኤርፖርቱ የሚንቀሳቀሱ መንገደኞች እንደሚቀንሱበት አስታወቀ፡፡በአለማችን በመንገደኞች ይጨናነቅ የነበረዉ ኤርፖርት በኮሮና ስጋት የተነሳ ስራዉ ቀዝቅዟል፡፡

~ በዩናይትድ ስቴትስ አትላንታ የሚገኘዉ ኧርትስፊልድ ጃክሰን ኤርፖርት በቀን 2‚600 በረራዎችን እና 63ሺ ሰዎች በኤርፖርቱ ይሰራሉ፡፡ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ እለታዊዉ በረራ ወድ 1‚200 ዝቅ ብሏል፤ስራዉ ተቀዛቅዟል፡፡

~ የሱዳን መዲና ካርቱም ከቀጣዩ ቅዳሜ አንስቶ ለሶስት ሳምንታት እንቅስቃሴን አገደች፡፡ዉሳኔዉ የኦምዱርማን ከተማንም እንደሚመለከተ የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ሳሊህ ተናግረዋል፡፡በሱዳን 4 ሞት ሲመዘገብ 29 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

~ በስፔን እና ኦስትሪያ በዛሬዉ እለት በከፊል ስራ ተጀምሯል፡፡በሺዎች የሚቆጠሩ ሱቆች በዛሬዉ እለት በኦስትሪያ ተከፍተዉ ዉለዋል፡፡በስፔን እንቅስቃሴ በከፊል መጀመሩ ነዋሪዎችን አስግቷል፡፡

~ በሶርያ በአማጽያኑ ግዛት አሊፖ የኮሮና ቫይረስ ስጋት አንዣቧል፡፡በአሊፖ በሞሃመድ ሻሂም ማኪኪ የህክምና ማዕከል ዉስጥ ብቻ ምርመራ የሚደረግ ሲሆን ግዛቱ የ3 ሚሊየን ሰዎች የመኖሪያ አካባቢ ነዉ፡፡

~ ባህሬን የመከላከያ ሆስፒታሏን የመኪና ማቆሚያ ስፍራን ወደ ጽኑ ህሙማን አስተኝቶ ማከሚያ ቀየረችዉ፡፡የመኪና ማቆሚያዉ ስፍራዉ 130 አልጋዎችን መያዝ ችሏል፡፡በባህሬን 1‚522 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ7 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ ሲንጋፖር በዛሬዉ እለት በጎዳና ላይ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያደርጉ አስገድዳ ዉላለች፡፡ያለ አፍና አፍንጫ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ሰዉ 300 የሲንጋፖር ዶላር ወይንም 212 የአሜሪካን ዶላር ይቀጣል፡፡

~ የብሩንዲ እግርኳስ ፌደሬሽን በሀገር ዉስጥ የሚደረጉ ስፖርታዊ ወድድሮችን አገደ፡፡አስቀድሞ ፌደሬሽኑ ጨዋታ እንደማያግድ ነገር ግን ተጫዋቾች በቫይረሱ እዳይያዙ እሰራለዉ ብሎ ነበር፡፡ብሩንዲ በአፍሪካ የመጨረሻዋ የእግር ኳስ ዉድድር ያገደች ሀገር ሆናለች፡፡በብሩንዲ 5 ግለሰቦች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *