መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 7፣ 2012 ዓ.ም

አጫጭር ዜናዎች

~ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ከብሄራዊ የሀገሪቱ አየር መንገድ የቀረበለትን 500 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የአፋጣኝ ድጎማ ጥያቄ እንደማይቀበል አስታወቀ፡፡አየር መንገዱ እ.ኤ.አ ከ2011 ጀምሮ ትርፍ የራቀዉ ሲሆን በኮሮና ስጋት 5ሺ ሰራተኞቹን ይዞ ለመቀጠል ተቸግሯል፡፡

~ በኮሮና የተነሳ ታንዛኒያ የአንድነት ቀን በዓል ክብረ በዓሏን ሰረዘች፡፡ይህ የታንዛኒያ የአንድነት ቀን ታንጋኒካ እና ዛንዚባር በጋራ በመሆን ታንዛኒያን የመሰረቱበት እለት ነዉ፡፡ቀኑን ለማክበር አስድሞ የተመደበዉ 500 ሚሊየን የታንዛኒያ ሽልንግ ለኮሮና መከላከል እንዲዉል ተደርጓል፡፡

~ በኬንያ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማያደርጉ ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀጡ ኬንያ አሳዉቃለች፡፡የቅጣቱ መጠን 20ሺ የኬንያ ሽልንግ ሲሆን አንድ ማስክ በገበያዉ ላይ በ100 ሽልንግ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

~ በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ የ523 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18,579 ደርሷል፡፡በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 172,541 ደርሷል፡፡

~ በስዊዘርላንድ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 973 ደረሰ፡፡በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 26,336 ደርሷል፡፡

~ በጀርመን እንቅስቃሴን የሚለክለዉ ህግ ለቀጣዮቹ 18 ቀናት መራዘሙን በዛሬዉ እለት ይፋ ተደረገ፡፡በጀርመን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 3,495 ደርሷል፡፡

~ በዴንማርክ የትምህርት ቤቶችን መከፈት የተቃወሙ እናቶች ተማሪዎች የጊኒ አሳማ ወይም የላብራቶሪ የመሞከሪያ አይጦች አይደሉም ሲሉ ተቃዉሞአቸዉን አሰሙ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *