መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 7፣ 2012 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የመንገደኞች አገልግሎት በረራውን በመቀነስ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ኢ.ዜ.አ ዘግቧል።
የካርጎ አገልግሎቱም ከአፍሪካ በተጨማሪ በአውሮፓና ቻይና ጭምር ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ፤ አየር መንገዱ ቀደም ሲል የካርጎ ጭነት አገልግሎት ሲሰጡ ከነበሩት አውሮፕላኖች በተጨማሪ 8 የመንገደኛ ማጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለካርጎ ስራ አሰማርቷል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *