በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 ደረሰ!
በተጨማሪ 7 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 – የ21 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 2 – የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ የጀርመን እና የቤልጂየም የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 3 – የ76 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከስዊድን የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።
ታማሚ 4 – የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከስዊድን የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 5 – የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከጃፓን የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 6 – የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊትና የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት እንዳላት በመጣራት ላይ ያለ።
ታማሚ 7 – የ61 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።