በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 111 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
በተጨማሪ 3 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 – የ11 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ፤ ከጅቡቲ የመጠና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 2 – የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።
ታማሚ 3 – የ15 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።