መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 19፣2012-ለእነ አቶ በረከት የክስ መዝገብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

በጥረት ኮርፖሬት የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት
የእነ አቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ ለሚያዚያ 26 /2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

በመዝገቡ ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል አቶ በረከት ስምኦንን፣ አቶ ታደሰ ካሳ እና አቶ ዳንኤል ይግዛው ይገኙበታል።

ግለሰቦቹ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሲጣራ መቆየቱና በክስ መዝገቡ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 19/2012 ዓ.ም. ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቀጥሮ ይዞ እንደነበር ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች በሌሉበት ዛሬ ባስቻለው ችሎትም የክስ መዝገቡን መርምሮ አለማጠናቀቁን አስታውቋል።
በተለይም ከጉዳዩ ስፋትና የቀረቡ ሰነዶች ብዛት አንፃር ለፍርድ ውሳኔ ጥራትና ፍትሃዊነት ሲባልም በቀነ ቀጠሮው ማድረስ እንዳልተቻለ ጠቅሷል።

ዳኞች ምርመራዎችን በማጠናቀቅ ሚያዚያ 26/2012 ዓ.ም. ለውሳኔ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

በዚሁ የቀን ቀጠሮም መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ተገቢውን ጥረት እንደሚያደርግም ገልጿል።
በተመሳሳይ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ጉዳያቸው እየታየ የሚገኘው በእነ አቶ ታደሰ ካሳ መዝገብም በቀጠሯቸው የሚታይ መሆኑን ጠቅሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *