
የውል ስምምነት የተፈረመላቸው ሰባት መንገዶች በጥቅሉ ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት አላቸው።
ለግንባታቸው የሚውለው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን መሆኑ ተገልጿል።
መንገዶቹ ከደብረ ብርሃን-ደነባ-ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር-ደነባ፣ ከፊቅ-ሰገግ-ገርቦ ደነን እንዲሁም ዮአሌ-ደነን፣ ከሁምቦ-ጠበላ-ዐባያ፣ ዳዬ-ግርጃ-ክብረ መንግሥት (መልካ ደስታ) እና ከመለያ-መጆ መገንጠያ፣ ከጅግጅጋ-ገለለሽ-ደጋሀምዶ-ሰገግ፣ ከሀወላቱላ-ወተርአራሳ-ያዩ-ውራቼ እና ከዛላአምበሳ-አሊቴና-መረዋ-ዕዳጋ ሐሙስ ናቸው።
መንገዶቹን ለመገንባት ከባለሥልጣኑ ጋር የውል ስምምነት ያደረጉት ተቋራጮች ስድስቱ አገር በቀል ሲሆኑ ፤ አንዱ የውጭ ተቋራጭ መሆኑ ታውቋል።
የመንገዶቹን ግንባታ ለማጠናቀቀም ከሦስት እስከ አራት ዓመታት እንደሚወስድ ተጠቅሷል።
ምንጭ፡-የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን