
ለአምራች ህብረት ስራ ማህበራት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብድር ተዘጋጅቷል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ለኢዜአ እንዳሉት፤ዓለምዓቀፉ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን የምጣኔ ሃብት ተጽዕኖ ለመቀነስ መንግስት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
የወረርሽኙን ተጽዕኖ ተቋቁመው ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲጨምሩ ”የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ለደንበኞቻቸው ብድር የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ በልማት ባንክ በኩል ያገኛሉ” ብለዋል።
እንደ ዶክተር ኢዮብ ገለጻ፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቀጥተኛ ተጎጂ ያደረጋቸው የንግድ ተቋማት በየወሩ ይከፍሉት የነበረው የተጨማሪ እሴትና የተርን ኦቨር ታክስን አጠራቅመው ሰኔ ላይ እንዲከፍሉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል።