መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 26፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የህንድ ፖሊስ በጉጃራት ለተቃዉሞ አደባባይ ከወጡ ዜጎች ጋር መጋጨቱ ተሰማ፡፡ ስደተኞቹ እንቅስቃሴ በመገታቱ ወደ ሀገራችን መሄድ አልቻልንም ሲሉ ተቃዉሞ አሰምተዋል፡፡በኒዉ ዴሊህ ከተማ ደግሞ በድብቅ አልኮል መሸጫ ስፍራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲጠጡ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡

~ ኢራን በ 132 የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ መስጊዶች በድጋሚ እንዲከፈቱ ዉሳኔ አሳለፈች፡፡ ዉሳኔዉ ግን በመዲናዋ ቴህራን እና በሺያ ቅዱስ ከተማ ማሻድ የሚገኙ መስጊዶችን አይመለከትም፡፡ በኢራን ከ6,200 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

~ ስፔን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለአለም አቀፍ ድጋፍ እንዲዉል የ125 ሚሊየን ዩሮ እንደምትሰጥ ቃል ገባች፡፡ ጠ/ሚ ፔድሮ ሳንቼዝ እንዳስታወቁት 50 ሚሊየን ዩሮ ለክትባት ምርምር የሚዉል ነዉ፡፡

~ የዩጋንዳ ዜጎች መንግስት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚያደርገዉ ጥረት 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርገዋል ተባለ፡፡

~ የእንግሊዝ ብሄራዊ ስትስቲክስ ቢሮ በሰራዉ አዲስ ጥናት እንቅስቃሴ በተከለከለባቸዉ ጊዜያት 50 በመቶ እድሜያቸዉ ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ብሪታኒያዉያን ለጭንቀት መዳረጋቸዉን ይፋ አደረገ፡፡

~ በደቡብ አፍሪካ ሰራተኞች ወደ ስራ እንዲመለሱ ፍቃድ ቢሰጥም አካላዊ ፈቀቅታን የመጠበቅ ግድታ እንዳለባቸዉ መመሪያ ተላለፈ፡፡

~ የሞቃዲሾ ከተማ ከንቲባ ኦማር ፊልሲ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ500 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር ከመደበኛዉ በላይ በመሆኑ ከኮሮና ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡በከተማዋ በሳምንት የሚመዘገበዉ ሞት ከ19 እስከ 49 ያህል ባለፉት ሁለት ሳምንት ነበር፡፡በሶማሊያ በኮሮና ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 32 ነዉ ተብሎ ሪፖርት ተደርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *