መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 26፣2012-ከጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸውን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባለፉት 9 ወራት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸው የገቢ ምርቶች ላይ ባካሄደው የጥራት ቁጥጥር ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆኑት ከደረጃ በታች በመሆናቸው ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል ብሏል፡፡

በቁጥጥሩ ከታገዱት የገቢ ምርቶች 2304.95 ሜ.ቶ ጥቅል ብረት፣ 28.7 ሜ.ቶ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣180 ካርቶን ሳሙና፣ 142 ካርቶን በፀሐይ ብርሀን የሚሰራ የእጅ ባትሪ፣150 ካርቶን የኤሌክትሪክ ገመድ እንዲሁም 43.22ሜ.ቶ የቆርቆሮ መስሪያ ጥሬ እቃ ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም 272 ጥቅል የአርማታ ብረት፣19770 ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት፣2934 ፍሬ የዉሃ ፓምፕ፣ 875 ካርቶን ባትሪ ድንጋይ አንዲሁም የታሸጉ ምግቦችና ሌሎችም የገቢ ምርቶች በቁጥጥሩ ወቅት ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *