መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 28፣2012-ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸዉ ያለዉን የድንበር ዉዝግብ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በመሪዎቻቸዉ በኩል አደረጉ፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና የሱዳን አቻቸዉ አብዱላ ሀምዶክ መካከል በትላንትናዉ እለት የስልክ ዉይይት በትላንትናዉ እለት መካሄዱን የሱዳን የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡ሱዳን በቅርቡ የኢትዮጲያ ወታደሮች አል ፋሻጋ ከተባለዉ ስፍራ እንዲለቁ ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል፡፡በሱዳን በኩል ያለዉ ስፍራ የግብርና እንቅስቃሴ የሚካሄድበት ነዉ፡፡ከ10 ቀናት በፊት በስፍራዉ በተሰነዘረ ጥቃት የአንድ ሱዳናዊ ወታደር ህይወት አልፏል፡፡ሶስት ደግሞ መቁሰላቸዉ የሚታወስ ሲሆን በታጣቂ ሀይል የተፈጸመ ጥቃት እንደነበር ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *