መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 28፣2012-የሚኒባስ ተጠቃሚዎች ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ የፊት መሸፈኛ ጭምብል መጠቀማቸው ግዴታ ነው ተባለ

የሚኒባስ ተጠቃሚዎች ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ የፊት መሸፈኛ ጭምብል መጠቀማቸው ግዴታ ነው ተባለ

ከመጭው ዓርብ ጀምሮ የሚኒባስ ተጠቃሚዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአስገዳጅነት መጠቀም እንዳባለቸው ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ ተናግረዋል፡፡

ተሳፋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጠቀም ሲንቀሳቀሱ ጭምብሎችን መጠቀም ይኖርባቸዋል ፣ ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የታክሲ አገልግሎቱን መጠቀም እንደማይችሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ለማድረግ አቅም የሌላቸው ግለሰቦችም ስካርፍ እና መሰል መሸፈኛዎችን የግድ መጠቀም እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡

ይህንን ተግባራዊ የማያደርጉ ተሳፋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መጠቀም እንደማይችሉና ቅጣት እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ የቅጣቱ አይነትም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስ ድርጅት ከዛሬ ጀምሮ ተሳፋሪዎች የአፍ መሸፈኛ ጭምብል በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ማስታወቁ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *