እዳው የተሰረዘላቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዚያ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ምህረት እንዲደረግላቸው መወሰኑን ተከትሎ ነው።
በዚህ መሰረት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ እዳ ያለባቸው እንዲሁም ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም ሂሳባቸውን የሚዘጉ የውሳኔው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ፍሬ ግብር፣ መቀጫ እና ወለድ ያለባቸው ተቋማት ዕዳ ሙሉ ለሙሉ መሰረዙም ነው የተገለጸው።
ከዚህ ባለፈም ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም ዕዳ ያለባቸው ተቋማትም ፍሬ ግብሩን በአንድ ጊዜ ከከፈሉ መቀጫና ወለድ እንደሚቀነስላቸው ተገልጿል።
ተቋማቱና ግለሰቦቹ ከሚከፍሉት ፍሬ ግብር ላይም የ10 በመቶ ቅናሽ የሚደረግላቸው ሲሆን ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው የተባለው።