መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 29፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ በዩናይትድ ኪንግደም ጥቁሮች ከነጮች አንጻር በኮሮና ቫይረስ ሁለት እጥፍ የመሞት እድል እንዳላቸዉ የብሄራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ አስታወቀ፡፡ጥቁር ወንዶችና ሴቶች ከነጮች አንጻር 90 በመቶ ለሞት መዳረጋቸዉ ተገልጿል፡፡

~ ጃፓን ለኢቦላ ህሙማን የሚሰጠዉን ረምድሲቪር የተባለ መድሃኒት ለኮሮና ህሙማን እንዲሰጥ ዉሳኔ አሳለፈች፡፡ባለፈዉ ሳምንት አሜሪካ ከኮሮና ቫይረስ ህሙማን ጋር በተያያዘ ለድንገተኛ አገልግሎት እንዲዉል ፈቅዷል፡፡በህንድና ፓኪስታን የሚገኙ የመድሃኒት አምራቾች ረምድሲቪር በብዛት በማምረት ይታወቃሉ፡፡

~ በደቡብ አፍሪካ የፓርላማ አባላት የኢንተርኔት ስብሰባ በበይነ መረብ ጠላፊዎች የተነሳ በወሲባዊ ቪዲዮ መጠለፉ ተሰማ፡፡የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሞዲሲ ቨርቹል ስብሰባ እንዳይደረግ ተቃዉማ ነበር፡፡

~ የአርጀንቲናዉ ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያደረጉት ጥረት እያሰመሰገናቸዉ ነዉ፡፡ከጎረቤት ሀገራት ቺሊ፣ፔሩ እና ብራዚል ያነሰ የቫይረሱ ስርጭት በአርጀንቲና ተመዝግቧል፡፡

~ የታንዛኒያዉ ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ከዉጪ የገቡ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ትክክለኛ አይደሉም ማለታቸዉን ተከትሎ የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ዉድቅ አደረገዉ፡፡

~ ራሺያ በኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከፈረንሳይና ከጀርመን በመብለጥ ከአለም 5ኛ ደረጃ ላይ በዛሬዉ እለት ተቀመጠች፡፡የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጊ ሶባይኒን የተጠቂዎች ቁጥር አሁን ከተገለጸዉ በ3 እጥፍ የበለጠ ነዉ ሲሉ ብለዋል፡፡በራሺያ 177,160 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

~ በመላዉ አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ስራ አጥ ዜጎች ቁጥር 33 ሚሊየን ደረሰ፡፡ባለፈዉ አንድ ሳምንት ዉስጥ ብቻ 3.2 ሚሊየን የሚጠጉ አሜሪካዉያን ስራ አጥ መሆናቸዉ ተመልክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *