
በ24 ሰዓት ዉስጥ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የ776 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 79,526 መድረሱን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ይፋ አድርጓል፡፡በአሜሪካ በ24 ሰዓት ዉስጥ ይመዘገብ ከነበረዉ ከ1000 እስከ 2500 ሞት አንጻር መቀነስ ታይቶበታል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከአሜሪካ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠችዉ ስፔን በአሜሪካ ያሉት የተጠቂዎች ቁጥር ከስፔን አንጻር ከአምስት እጥፍ በላይ ደርሷል፡፡