መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 4፣2012-የአለም የጤና ድርጅት 7 ወይንም 8 የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት እዉን ለማድረግ በፍጥነት እየተሰራ መሆኑን አስታወቀ

የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚና የማህበራዊ ምክር ቤት ጋር በቪዲዮ በነበራቸዉ ዉይይት እዳስታወቁት 7 ወይንም 8 የሚሆኑ የቫይረሱ የክትባት መድሃኒት በእጩነት በመምረጥ የምርምር ስራዉ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታዉቀዋል፡፡

በትላንትናዉ የቪዲዮ ኮንፍረንስ ላይ እንደተገለጸዉ ባሳለፍነዉ ሳምንት ከ40 የአለም ሀገራት፣ተቋማትና ባንኮች ለክትባቱ፣ለምርምር ስራ በተለገሰዉ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ስራዉ የሚከናወን ሲሆን ተጨማሪ ፈንድ እንደሚያስ ፈልግ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል፡፡

ለኮሮና ቫይረስ ክትባት በሚል ከ100 በላይ እጩ የምርምር ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል እጅግ የተሸሉ የተባሉ 7 ወይንም 8 መለየታቸዉን የአለም የጤና ደርጅት አስታዉቋል፡፡ተለዩ ስለተባሉት የክትባት መድሃኒት ግን ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *