መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 4፣2012-በአራዳ ክ/ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ክልከላውን ተላልፈው የተገኙ ግለሰቦች ከ48 ሺ ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተቀጡ የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ ፡፡

ሚያዚያ 3/2012 ዓ.ም በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 2 እና 5 ሮዛ እና ገዳም ሰፈር እየተባሉ በሚጠሩ አካባቢዎች በአነስተኛ ጠባብ ክፍል ውስጥ 24 ሰዎች ተሰባስበው ሺሻ ሲያጨሱ ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ተሰባበሰበው ጠጅ ሲጠጡ የተገኙ 18 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን ሢያስጠቅሙ የተገኙ ግለቦችንም ምርመራ
እየጣራባቸው እንደሚገኝ ምክትል ኢንስፔክተር ፍቃዱ አዴቮ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የራስ ደስታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የማስተባበሪያ ሃላፊ ተናግረዋል፡፡

የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከወጣ ጀምሮ በተወሰዱ እርምጃዎችም በ11 መዝገቦች 15 ተከሳሾችን በመያዝ ከ48 ሺ ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት ማስቀጣታቸውን ምክትል ኢንስፔክተር ፍቃዱ አዴቮ አብራርተዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *