መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 5፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የላይቤሪያን ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃን አስተዳደር የተቸዉ የፌስቡክ ተጠቃሚ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ግለሰቡ መንግስት በኮሮና ቀዉስ ዘመን ለእኛ ሩዝ ሳይሆን AK-47 ሽጉጥ ነዉ የሚያስፈልገን ሲል ጽፏል፡፡ግለሰቡ ሽብርን ለመፍጠር አይደለም ቢልም ተቀባይነት አላገኝም፡፡

~ ኒጀር መስጊዶችና ቤተ ክርስቲያኖች በድጋሚ እንዲከፈቱ ፈቀደች፡፡በሀገሪቱ በኮሮና ቀዉስ የተነሳ ለሁለት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ተዘግተዉ ቆይተዋል፡፡854 ሰዎች በሀገሪቱ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

~ ሲንጋፖር የአሜሪካ ዜግነት ያለዉ የአዉሮፕላን አብራሪ የግዳጅ ለይቶ ማቆያ ህግን በመተላለፉ በአራት ሳምንት እስር ቀጥታለች፡፡አብራሪዉ ከአዉስትራሊያ ከመጣ በኃላ በሆቴሉ ተገድቦ እንዲቀመጥ መመሪያ ቢሰጠዉም ይህንን በመጣስ በገበያ ስፍራ ተገኝቷል፡፡

~ የአለም የጤና ድርጀት ከፍተኛ ሙሁራን ዓለም ከኮሮና ቫይረስ ቀዉስ ለመዉጣት ገና ረጅም መንገድ ይቀራታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡የድርጅቱ የድንገተኛ ፕሮግራም ዶ/ር ማይክ ሬይን የቫይረሱ ስርጭት አሁንም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

~ የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የህንድን ኢኮኖሚ ለመደገፍ የ264 ቢለየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ለኢኮኖሚዉ ማድረጋቸዉን አስታወቁ፡፡

~ ካዛኪስታን ከቀጣይ ሰኞ አንስቶ የእምነት ተቋማትና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን እንደምትከፍት አስታወቀች፡፡የሀይማኖት ተቋማት ማስተናገድ የሚችሉት ከሚያዙት 30 በመቶ ያህሉ ነዉ፡፡ከ5ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ 19 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር ባቢስ ሀገሪቱን ከኦስትሪያና ስሎቫኪያ የሚያዋስኑ ድንበሮች በወርሃ ሰኔ ሊከፈቱ እንደሚችሉ አስታወቁ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *