መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 7፣2012-የናምቢያ ፕሬዝዳንት አዳዲስ ተሸከርካሪዎችን የመንግስት ባለስልጣናት እንዳይገዙ መመሪያ አስተላለፉ

ከፕሬዝዳንት ሀጌ ጊንጎብ በተላለፈዉ መመሪያ መሰረት ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ሚንስትሮች አዳዲስ ተሸከርካሪን እንዳይገዙ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ለቅንጡ ተሸከርካሪዎች ይዉል የነበረዉ ገንዘብ ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ እንዲሆን ፕሬዝዳንቱ መወሰናቸዉን በቲዉተር ገጻቸዉ ይፋ አድርገዋል፡፡

ይህ ዉሳኔ 10.7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከብክነት ይታደጋል፡፡ከኮሮና ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥመዉ የጤና ችግር እና ለኢኮኖሚ ድጋፍ ይዉላል፡፡ለነዳጅ ለባለስልጣናት የሚሰጠዉ ገንዘብ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡2.5 ሚሊየን ህዝብ ባላት ናሚቢያ 16 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እንዳሉ ሲነገር ሞት ሪፖርት አልተደረገም፡፡

በናሚቢያ ሁሉም ሚንስትርና ምክትሎቻቸዉ እንደተሾሙ መርቼዲስ ቤንዝ መኪና ይሰጣቸዋል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *