መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 10፤2012-በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ጉና በጌምድር ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ የወረዳው የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ጉዳት ደረሰ

ግንቦት 07 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ላይ በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ 1500 ሰዎችን መያዝ የሚችለው የወረዳው የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ጉዳት መድረሱን በቦታው ተገኝተን ዘግበናል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቀ ዘመነ የወረዳው አመራር ሳይደናገጥ ወደ ስራ በመግባት አዳራሹ ተመልሶ የሚገነባበት መፍትሄ መፈለግ እንዳለበት ገልፀዋል።

አክለውም አደጋው በዋናነት በተፈጥሮ አደጋ የተከሰተ ቢሆንም ለዚህ አደጋ ተጋላጭነት ምክንያቶችን በሂደት በመለየት ለህዝብ ማሳወቅ ይገባል ብለዋል።

© የደ/ጎ/ዞን/የመ/ኮ/ጉዳዮች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *