መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 10፤2012-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ የካሳ ክፍያ እንደሚጠብቅ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ላይ ለደረሰው አደጋ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ከኩባንያው ካሳ እንደሚጠብቅ ተናግረዋል።

አቶ ተወልደ ከሬውተርስ ጋር ባደረጉት ቆይታ አየር መንገዱ ቦይንግን በካሳ ክፍያው ዙሪያ ለውይይት እንደጋበዘው ጠቅሰው፥ ካሳው ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ለደረሰው ጉዳት መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም አየር መንገዱ ከኩባንያው እንዲቀርቡለት ያዘዛቸውና በጊዜ ባልተረከባቸው አውሮፕላኖች ሳቢያ ያጣውን ገቢ ታሳቢ ያደረገ ይሆናልም ነው ያሉት አቶ ተወልደ።

ዋና ስራ አስፈጻሚው የካሳ ክፍያውን የበጀት አመቱ መዝጊያ በሆነው ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚጠብቁም ነው የተናገሩት።

የካሳውን መጠን ያልጠቀሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ካሳው በገንዘብ አልያም በአውሮፕላን እቃ አቅርቦት መልክ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *