መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 11፤2012-ሲንጋፖር በስህተት የኮሮና ቫይረስ አለባችሁ ያለቻቸዉን 357 ሰዎች ይቅርታ ጠየቀች


የሲንጋፖር የጤና ሚንስትር በአጭር የጹሁፍ መልዕክት የኮሮና ቫይረስ አለባችሁ ብሎ ካሳቀወቃቸዉ ዜጎች መካከል የ357ቱ በስህተት እንደሆነ አስታዉቋል፡፡ስህተቱ ሊፈጠር የቻለዉ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ነዉ፡፡
ይህንኑ ተከትሎ ቫይረሱ አለባችሁ በሚል መጨናነቅ ለተፈጠረባቸዉ ግለሰቦች መንግስት ይቅርታ ጠይቋል፡፡ሲንጋፖር ከ28ሺ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲጠቁ የ22ቱ ህይወት አልፏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *