መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 12፤2012-ብሩንዲ በዛሬዉ እለት ሀገር ሀገር አቀፍ ምርጫ ስታከናዉን የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋቷ ተሰማ

የኢንተርኔት አገልግሎቱ በማህበራዊ ገጽ ትስስር መተግበሪዎች ቲዉተር፣ፌስቡክ እና ዋትአፕ መቋረጡ ይፋ ተደርጓል፡፡የቪፒኤን ተጠቃሚዎች አገልገሎቱን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እነማን እንደሆኑ በግልጽ የሚያሳይ ነዉ፡፡የብሩንዲ መንግስት በጉዳዩ ላይ የሰጠዉ ማብራሪያ የለም፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች የኢንተርኔት መቋረጡን በመተቸት የመረጃ ፍሰት ላይ ተጽእኖ እንደሚሳድር ተናግረዋል፡፡የምርጫ ጣቢያዎች ከማለዳ ጀምሮ ለመራጮች ክፍት ተደርገዋል፡፡ አምስት ሚሊየን የሚጠጉ መራጮች ድምጽ በመስጠት ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡ሰባት የፕሬዝዳንት እጩዎች ፕሬዝዳንት ፔሪ ኒኩሪንዚዛን ለመተካት ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ይገኛል፡፡

በምርጫ ጣቢያ ዉስጥ ለታዛቢዎች ስልክ እና ካሜራ መያዝ ቢከለከልም 53 ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን አስቀድሞ መናገሩ ይታወሳል፡፡በዛሬዉ ምርጫ ፕሬዝዳንት፣የህዝብ እንደራሴዎች እና የከተማ መስተዳድር የምክር ቤት አባላት የሚመረጡበት ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *