በረራው የኮሮና ቫይረስን ለመመከት ለፍልስጤም የረድኤት ድጋፍ ለማድረስ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና በእስራኤል መካከል የንግድ በረራ በይፋዊ መልኩ ተደርጎ የማያውቅ ሲሆን ይህንን የመጀመሪያ አድርጎታል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና እስራኤል ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የሌላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ 14ቶን የጫነው የኢትሃድ አውሮፕላን በቴላቪቭ ቤን ጉሪኦን ኤርፖርት ስለመድረሱ እስራኤል ማረጋገጫ ሰጥታለች፡፡
ኤምሬትስ ከእስራኤል ጋር የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ያልመሰረተች ሀገር ስትሆን በሚስጥር የእስራኤል አጋር ናት በሚል በቱርክና ኢራን ትወነጀላለች፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ