መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 12፤2012-የኮሮና ቫይረስ ህሙማንን የሚያግዝ ሮቦቶችን ሩዋንዳ ተረክባለች

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የምግብና ፣ የመድሃኒት ድጋፍ በማድረግ የሚያግዙ አምስት ሮቦቶች መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ሮቦቶቹ አገልግሎቱን ሲሰጡ ህሙማን እና ዶክተሮች በቪዲዮ ኮንፈረስ አማካኝነት ይገናኛሉ፡፡ ለሮቦቶቹ ሚዊዛ ፣ ኒጋቦ ፣ አካዙባ ፣ አኪዚሪ እና ዩሪሚ የሚባሉ ስያሜዎች ተሰጥቷቸዋል፡፡

የሩዋንዳ የጤና ሚኒስትር ዳኔል ናጋሚጂ የሮቦቶቹ ዋንኛ ዓላማ የጤና ባለሙያዎች ድካም በማቃለል ለቫይረሱ ያላቸው ተጋላጭነት ለመቀነስ ነው ብለዋል፡፡

ከአምስቱ ሮቦቶች በተጨማሪ ሌሎች ሮቦቶች ያስፈልጉናል ብለዋል፡፡ ሩዋንዳ ሮቦቶቹን በቤልጂየም ከሚገኝ ኩባንያ ተረክባለች፡፡
በደቂቃ ከ 50 እስከ 150 ሰዎች የመለየት ፣ መረጃ የመቅዳትና የማከማቸት ስራን ያከናውናል፡፡

በሩዋንዳ 297 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ 203ቱ አገግመዋል፡፡ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረሱ ህልፈት እስካሁን አልተመዘገበም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *