መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-በኢራን 10ሺ የሚጠጉ የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ተሰማ


የኢራን ምክትል የጤና ሚንስትር ቋሲም ጃንባባአይ እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስን በመካላከል ላይ የነበሩ 10ሺ የሚጠጉ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ስለመጠቃታቸዉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡በወርሃ ሚያዚያ መጀመሪያ ከ100 በላይ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ኢራን ስታሳዉቅ በአሁኑ ሪፖርት የሟቾች ቁጥር አልተካተተም፡፡
ከ129ሺ በላይ ሰዎች በኢራን በቫይረሱ ሲጠቁ የ7,249 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ኢራን የኢድ አልፈጥር በዓልን በማስመልከት የሚደረጉ ጉዞዎች እንዳይከናወኑ መመሪያ ማሳለፏ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *