መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 13፤2012-በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የስድስት ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገሬ አትግቡ ያለችዉ ካምቦዲያ እገዳዉን አነሳች

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መዛመቱን ተከትሎ የካምቦዲያ መንግስት ከስድስት ሀገራት የሚመጡ ቱሪስቶች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ መከልከሉ ይታወሳል፡፡ሀገራቱ ጣልያን፣ኢራን፣ጀርመን፣ስፔን፣ፈረንሳይ እና ዩናይትስ ስቴትስ ናቸዉ፡፡

የካምቦዲያ የጤና ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ እገዳዉ መነሳቱን በመግለጽ ወደ ካምቦዲያ የሚመጡ ቱሪስቶች ከ72 ሰዓታት ያልበለጠ ከቫይረሱ ነጻ ስለመሆናቸው የሚያሳይ የምስክር ወረቅት እና የ50ሺ የአሜሪካ ዶላር የጤና መድህን ሽፋን በሟሟላት መምጣት እንደሚችሉ ይፋ አድርገዋል፡፡

ይህንን ሁሉ መስፈርቶች ቱሪስቶች ካሟሉ በኃላም ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ዉስጥ የመሆን ግዴታ አለባቸዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *