
በሙምባይ ምዕራባዊ ከተማ በሚገኘው ሎክማንያ ቲላክ ሙኒሲፓል ሆስፒታል ውስጥ በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ እናቶች ከ 100 በላይ ጤነኛ ህፃናት መወለዳቸው ነው የተሰማው፡፡
115 ከሚሆኑ የቫይረሱ ተጠቂ እናቶች ከተገኙት ህፃናት መካከል ደግሞ ሶስቱ በቫይረሱ ተጠቅተው የነበረ ሲሆን ፤ በተደረገላቸው ክትትል ከቫይረሱ ማገገማቸው ተጠቁሟል፡፡
የተወለዱት ህፃናትም 56ቱ ወንዶች 59ኙ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ሁለት ቫይረሱ ያጠቃቸው እርጉዝ ሴቶች በሆስፒታሉ ሳሉ ህይወታቸው ሲያልፍ ፤ አንደኛዋ ሴት ግን ልጇን ወደዚህ ዓለም ከላከች በኋላ ነበር። ሕይወቷ ሊያልፍ የቻለው
65 ዶክተሮችና 24 ነርሶች በዚሁ የማዋለድ ስራ ላይ ተሳታፊ ሁነዋል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ