መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 14፤2012-በግብጽ ከሚገኙ ሰራተኞች 1በመቶ ከደሞዛቸዉ በመቁረጥ ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ ሊዉል ነዉ


የኮሮና ቫይረስ ቀዉስ የሚያስከትለዉን የኢኮኖሚ ጉዳት ለማካካስ እንዲቻል በሀገሪቱ ከሚገኙ የደሞዝ ሰራተኞች 1በመቶ ከደሞዛቸዉ ለመቁረጥ የሚያስችል መመሪያ ይፋ ተደረገ፡፡መመሪያዉ ከወርሃ ሀምሌ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
ይህ መመሪያ ወርሃዊ ደሞዛቸዉ ከ125 የአሜሪካን ዶላር በታች ያሉ ዜጎችን እንደማይመለከት የግብጽ መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡በግብጽ ከ15ሺ በላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ሲኖሩ ከነዚህ መካከል የ696 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *