~ የታንዛኒያ ዳሬሰላም ኮሚሽነር ፖል ማኮናዳ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስላበቃ የፊታችን እሁድ አደባባይ በመዉጣት ደስታችንን እንግለጽ ሲሉ ያስተላለፉት መልዕከት ተቃዉሞ አስነሳ፡፡በታንዛኒያ 509 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቃ የ21 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡
~ በኮሎምቢያ በሚሊየን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብን አላግባብ ያባከኑ የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ለኮሮና ቫይረስ ለሆስፒታል ቁሳቁስና ለምግበ ግዢ የተመደበ ገንዘብ ማናከናቸዉ ተረጋግጧል፡፡
~ ሳዑዲ አረቢያ እና ኢምሬቶች የኢድ እለት መስጊዶች ዝግ እንደሚሆኑ ይፋ ተደረገ፡፡በአንጻሩ ስፔን በበኩሏ በማድሪድ ከሰኞ ጀምሮ በከፊል እንቅስቃሴን የሚከለክለዉ ህግ ከሰኞ ጀምሮ እንደሚነሳ አስታዉቃለች፡፡
~ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወባ መድሃኒት የሆነዉ ሀይድሮክሲክሎሪኪዊን አጋዥ ነዉ ማለታቸዉን ተከትሎ በናይጄሪያ የመድሃኒቱ ሽያጭ መጨመሩ ተሰማ፡፡የትራምፕን ንግግር ላሰንት የህክምና ዘገባ አጣጥሎታል፡፡
~ የጉበት ህሙማን በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ ለሞት የመዳረግ እድላቸዉ ከፍተኛ መሆኑን የኦክስፎርድ እና የሰሜናዊ ካሮላይና ባጠኑት ሪፖርት መረጋገጡ ይፋ ተደርጓል፡፡
~ በስፔን ዝቅተኛ ገቢ ባለባቸዉ ግዛቶች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከሀብታም የሀገሪቱ ግዛቶች በአምስት እጥፍ የበለጠ መሆኑ ተሰማ፡፡27‚940 ሰዎች በስፔን በቫይረሱ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡
~ በማይናማር ምስራቃዊ ካሪን ግዛት በኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዘገበ ሲል ያሰራጨዉ የዜና አርታኢ መረጃዎ የሀሰት ነዉ በሚል የሁለት ዓመት የእስር ትዕዛዝ ተላለፈበት፡፡
በስምኦን ደረጄ