መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 15፣2012-በስፔን በተሸከርካሪ የታጀበ የተቃዉሞ ሰልፍ ተካሄደ

የስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝና ምክትላቸዉ ፓብሎ ኢግላሲያስ ለኮሮና ቫይረስ ቀዉስ ሁነኛ መፍትሄ አልሰጡም ያሉ ሰልፈኞች በማድሪድ ጎዳና በመኪና ዉስጥ ሆነዉ ተቃዉሞ አሰምተዋል፡፡ተቃዉሞ በቀኝ ዘመሙ ቮክስ ፓርቲ የተሰናዳ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ታድመዋል፡፡

በስፔን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ጥብቅ መመሪያዎች ስርጭቱ መቀነሱን ተከትሎ ማሻሻያ ቢደረግም በማድሪድና ባርሴሎና ከተሞች ግን የስርጭቱ መጠን ለዉጥ ባለማሳየቱ ጥብቅ መመሪያዉ ቀጥሏል፡፡ይህ ደግሞ ለስራ አጥነት ዳርጎናል ያሉ ሰልፈኞች ተቃዉሞ አሰምተዋል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *