መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 15፣2012-በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች 62% የሚሆኑት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 62 ፐርሰንት የሚሆኑት ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 494 ሰዎች ውስጥ 304 ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ፣ በተለይ በልደታና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ይበልጥ መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡

ከልደታ ክ/ከተማ 104 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱ ነው የተገለጸው፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በተስፋፋባቸው ክ/ከተሞች የእንቅስቃሴ እገዳ ሊደረግ እንደሚችል ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክ/ከተሞች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከክልሎች ደግሞ ከጋምቤላ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸውን ዶ/ር ሊያ ገልጸዋል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *