መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 15፣2012-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል

ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፎአል፡፡በዚሁ መሠረት

– ከ1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆን

ከ2008 – 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር በቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፎአል፡፡

በሌላ በኩል የከተማዋን ገቢ ለማሻሻል ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያላቸውን አቅም በዝርዝር ፈተሸው ለከተማዋ ገቢ እድገት በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ዙሪያና አፈፃፀሙንም የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መንገድ ላይ ተወያይቷል።

የታክስ መሰረትን በማስፋትም በተለይም ማዘጋጃቤታዊ እና የከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅምና የአስራር በተሻለ መልክ በማደራጀት የ2013 ዓም በጀት በመካከለኛ ገቢ ምጣኔ መሰረት ተዘጋጅቶ ለውይይት እንዲቀርብ ተወስኗል።

ምንጭ፦ከንቲባ ፅ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *