መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 15፤2012-ኢድ ሙባረክ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በመሉ እንኳን ለ1441ኛው ዒድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም ፣ የጤና ፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

በዓሉን አስመልክቶ ከቀኑ 6:00-8:00 ሰዓት ልዩ ልዩ ፕሮግራም በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት 101.1 ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ ላይ አዘጋጅተንላችኋል።

በፕሮግራሙ መካከል በደደቢት ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ በድሬዳዋ ከተማና በብሄራዊ ቡድን ውስጥ በግራ ተመላላሽ ስፍራ ላይ ድንቅ ብቃቱን ማስመስከር ከቻለው አህመድ ረሺድ (ሺሪላ) ጋር ጥሩ ቆይታ ይኖረናል።

በተጨማሪም በሀዲያ ሆሳዕና የተጫወተውና በጅማ አባጅፋርና በመቐለ ከተማ ክለቦች የሊጉ ሻምፒዮና ክብርን አብሮ መቀዳጀት የቻለው የተከላካይና ፣ አማካይ ስፍራ ተጫዋች አሚኑ ነስሩ ጋር ጎራ እንላለን።

የመጨረሻ እንግዳችን በቅዱስ ጊዮርጊስ (ፈረሰኞቹ) ቤት ገና ከለጋ እድሜው ከተስፋ ቡድን ጀምሮ በ2007 የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን ሀ ብሎ መሰለፍ እስከጀመረበት ክለቡን በታማኝነት እያገለገለ የሚገኘውና ፤ በግብ ማስቆጠር ላይ ለብሄራዊ ቡድኑ ስኬት ተስፋ የተጣለበት አቡበከር ሳኒ ጋር ቆንጆ ቆይታ ይኖረናል ታደምጡን ዘንድ የአክብሮት ግብዣችን ነው።ሚኪያስ ጸጋዬ እና ስምኦን ደረጄ እንጠብቃችኃለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *