መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 16፤2012-በሆንግ ኮንግ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ተቃዉሞ ለማሰማት በዛሬዉ እለት አደባባይ ወጥተዋል

በቤጂንግ አስተዳደር የተዘጋጀዉን ብሄራዊ የደህንነት ረቂቅ ህግ ሰልፈኞቹ ተችተዋል፡፡ህጉ የአለም አቀፍ መንግስታትና የሰብዓዊ መብትን የሚጻረር ነዉ በሚል ተተችቷል፡፡በሆንግ ኮንጎ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ከስምንት ሰዉ በላይ ሆኖ መሰብሰብ ባይፈቀድም ይህንን በመጣስ ዜጎች አደባባይ ወጥተዋል፡፡

ሆንግ ኮንግ ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ብሪታኒያ እ.ኤአ በ1997 ለቻይና ተላልፋ ብትሰጥም አንድ አገር ሁለት አስተዳደር በሚል መመሪያ ትተዳደራለች፡፡የቤጂንግ ባለስልጣናት መብትን ይገድባል በሚል ወቀሳ በሚቀርብበት ህግ ዙርያ የሆንግ ኮንግን ሉዐላዊነት የሚጻረር አይደለም ሲሉ ያስተባብላሉ፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *