
በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 655 ደርሷል፡፡
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-
~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ2844 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 73 ኢትዮጲያዉያን ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡
~ 49ኙ ወንዶች ሲሆኑ 24ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።እድሜያቸዉ ከ6 እስከ 75 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።
~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 56 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 4 ሰዎች ትግራይ ክልል፣3ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች፣2 ከአማራ ክልል፣8 ከሶማሌ ክልል
~ 27 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡
~ 15 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላቸዉ፡፡
~ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ 31 ሰዎች ናቸው።
ተጨማሪ መረጃ ፦
~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 83,854 ደርሷል።
~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 7 ሰዎች አገግመዋል።
~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 159 ደርሰዋል።
~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ አንድ ታማሚ አለ ፡፡
~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 489 ናቸው።
~ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡