በኢትዮጲያ ሰባተኛ ሞት ተመዝግቧል
በተጓዳኝ ህመም ምክንያት ህክምና ላይ የነበሩ የ70 ዓመት እድሜ ያላቸዉ አዛዉንት ሴት በኮሮና ቫይረስ በተደረገ ምርምራ ናሙና ከተወሰደ በኃላ የምርመራ ዉጤት ሳይደርስ ህይወታቸዉ ቢያልፍም በዉጤቱ በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ተረጋግጧል፡፡
በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል፡፡
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-
~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ4950 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 98 ኢትዮጲያዉያን ሲሆኑ አንድ የብሩንዲ ዜጋ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡
~ 53ቱ ወንዶች ሲሆኑ 47ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።እድሜያቸዉ ከ3 እስከ 70 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።
~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 94 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰዉ ትግራይ ክልል፣3 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣2 ሰዎች ከሶማሌ ክልል
~ 3 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡
~ 35 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላቸዉ፡፡
~ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ 62 ሰዎች ናቸው።
ተጨማሪ መረጃ ፦
~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 96,566 ደርሷል።
~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 10 ሰዎች አገግመዋል።
~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 191 ደርሰዋል።
~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ አንድ ታማሚ አለ ፡፡
~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 631 ናቸው።
~ የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡