መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 21፣2012-ትራምፕ ለናይጄሪያ እንደሚልኩ ቃል የገቡት አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ አለመድረሱ ተሰማ

የናይጄሪያ የመረጃ ሚንስትር ከአሜሪካ ቃል የተገቡት መሳሪያዎችን ሀገራቸዉ አለመረከቧን ገልጸዋል፡፡ሚንስትሩ ላ ሞሃመድ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 1000 አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያን ለምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መላካቸዉን ቢናገሩም ናይጀሪያ ግን የተረከበችዉ መሳሪያ አለመኖሩን ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

ባለፈዉ ሳምንት በሚቺጋን በፎርድ ሞተር በነበራቸዉ ቆይታ ለናይጀሪያ 1000 የአጋዥ መተንፈሻ መሳሪያ ስለመላካቸዉ መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡ናይጀሪያ ግን የተቀበልኩህ መሳሪያ የለም ስትል አስተባብላለች፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *