መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 21፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በፓኪስታን የሚገኝ የመድሃኒት ኩባንያ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን የሚያግዝ መድሃኒትን ከባንግላዲሽ ሊያስመጣ መሆኑን አስታወቀ፡፡በአሜሪካና ጃፓን ለጽኑ ህሙማን እንዲሰጥ ፍቃድ የተሰጠዉን ረምዲሲቪር የተሰኘዉን መድሃኒት ነዉ፡፡በፓኪስታን ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ የተባለዉ የ56 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ ክሮሺያ ለ10 ሀገራት ድንበሯን ክፍት እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡ሆኖም ወደ ክሮሺያ የሚመመጡ ጎብኚዎች ከኮሮና ቫይረስ ነጻ የተባሉበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

~ ግሪክ ከ17 ቀናት በኃላ ከ29 ሀገራት ለሚመጡ ቱሪስቶች በሯን ክፍት ልታደርግ ነዉ፡፡የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተስፋፋባቸዉ እንግሊዝ፣ፈረንሳይ፣ስፔንና ጣልያን ለጊዜዉ ቱሪስቶች እንዳይመጡ ግሪክ ከልክላለች፡፡

~ በናይጀሪያ የሚገኙ ሆስፒታሎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋትን ተከትሎ በተለያየ ህመም የሚመጡ ሰዎችን እያገለሉ መሆኑ ተሰማ፡፡ከሆስፒታል በራፍ በርካቶች እየተመለሱ መሆኑን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡የቫይረሱ ተጠቂዎች በሀገሪቱ 9ሺ ደርሷል፡፡

~ በቻይና የሚደገፈዉ የእስያ የመሰረተልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፊሊፒንስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያሳደረባትን ተጽእኖ ለመከላከል ለምታደርገዉ ጥረት 750 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብድር ሊሰጣት ነዉ፡፡

~ በ24 ሰዓት ዉስጥ የ232 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ያደረገችዉ ሩሲያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገሪቱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

~ በቱርክ ከ2 ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬዉ እለት የሰዉ ቁጥር በተገደበበት መልኩ የእምነት ስፍራ ክፍት ተደርጓል፡፡የጁማ የጸሎት ስነስርዓት ተከናዉኗል፡፡ከ160ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ የ4,461 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *