
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ራሺያ በድጋሚ የቡድን ሰባት አባል እንድትሆን ላቀረቡት ጥያቄ ካናዳ ድጋፍ እንደማትሰጥ አስታውቃለች።ራሺያ አለምአቀፍ ህጎችን ተግባራዊ ለማድረግ አሁንም ፍቃደኛ አይደለችም ሲሉ የካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ተናግረዋል።
ራሺያ በ2014 ከዩክሬን ክሪሚያን በህዝበ ውሳኔ ወደ ራሷ መጠቅለሏ ከቡድን 7 እንድትወገድ ምክንያት ሆኗል።ትራምፕ የቡድን ሰባት ቀጣይ ስብሰባ እስከ መስከረም ይራዘም በስብስቡ ላይ ሩሲያ፣አውስትራሊያ፣ህንድና ደቡብ ኮርያ ይጋበዙ ሲሉ ተናግረዋል።
ስምኦን ደረጄ