መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 24፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ አሜሪካ ከአለም የጤና ድርጅት ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጣለው ማለቷን ቻይና ተቸች። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ሊጅአን አሜሪካ ራስ ወዳድ አስተዳደሯም ሀላፊነት አይሰማውም ብለዋል።

~ በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ ሞት አልተመዘገበም። በአንፃሩ በኢራን በሁለት ወር ውስጥ ከፍተኛ የተባለ የቫይረሱ ስርጭት ሲመዘገብ ባለፉት 24 ሰዓት 2,979 ሰዎች ተጠቅተዋል።

~ በደቡብ አፍሪካ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ተጥሎ የነበረው የአልኮል ሽያጭ ክልከላ ተነሳ።ከሁለት ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተፈቅዷል።

~ ዩጋንዳን ከደቡብ ሱዳን የሚያዋስናት ድንበር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መዘጋቱን በመቃወም ሰልፍ ከወጡ ሰዎች መካከል ሁለቱ የፓርላማ አባላት ሲሆኑ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው አስታውቋል።

~ የራሺያ መዲና ሞስኮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ ያስቀመጠችውን ክልከላ ከ9 ሳምንት በኋላ በዛሬው እለት አነሳች። በግሪክና ፖርቹጋል ደግሞ ሲኒማ ቤቶች ዳግም ተከፍተዋል።

~ በቺሊ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 100ሺ እየተጠጋ ሲሆን ፤ በጎረቤቷ ቦሊቪያ ከተመዘገበው በአስር እጥፍ የበለጠ ሆኗል። ቦሊቪያ በአንፃሩ እንቅስቃሴ የሚከለክሉ ህጎች ላይ በዛሬው እለት ማሻሻያ አድርጋለች።

~ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ማረሚያ ቤት ውስጥ የነበረ የኦማን ዜግነት ያለው ሰው ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘበት። ድርጊቱን ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ኢምሬትስ የታራሚዎችን ቁጥር እንድትቀንስ ጫና እያደረጉ ይገኛል።

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *