
በጥንታዊቷ እየሩሳሌም ከተማ የ 32 ዓመቱ ያልታጠቀው ፍልስጤማዊ ኢያድ ኬሀያሪ በእስራኤል ወታደር ተተኩሶበት ህይወቱ አልፏል፡፡
ጉዳዩ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጥረትን የፈጠረ ሲሆን የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር ቤን ጋንታዝ ‹‹ለተገደለው ፍልስጤማዊ እጅግ በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን ፤ የቤተሰቡን ሀዘን የምንጋራው ይሆናል ጉዳዩም ይጣራል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታናሁ ዝምታን መርጠዋል፡፡
በዮርዳኖስ ሸለቆ አካባቢ አይሁዶችን የማስፈር ፖሊሲ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጥረት መፍጠሩን ቀጥሏል፡፡
ድርጊቱን እስራኤል ከአሜሪካ አረንጓዴ መብራት ብታገኝበትም ፍልስጤም ፣ የአረብ ሀገራት ፣ የተ.መ.ድ እና በርከት ያሉ የአውሮፓ ሀገራት እየተቹት ይገኛል፡፡
በስምኦን ደረጄ