
የዓለም የጤና ድርጅት ለኮቪድ-19 ህሙማን ይህንን የፀረ ወባ መድሃኒት ሀገራት ከመጠቀም እንዲያቆሙ ቢያደርጉም አንዳንድ ሀገራት ግን ክልከላውን በመጣስ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡
የዩኤስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ይህንን የፀረ ወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይጠቀሙ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡
የብራዚሉ አቻቸው ጄር ቦልሴናሮ በበኩላቸው የ 93 ዓመት እድሜ ያላት ወላጅ እናቴ የፀረ ወባ መድሃኒቱ ካስፈለጋት ብዬ በሳጥን ውስጥ ገዝቼ አስቀምጫለው ብለዋል፡፡
የፀረ ወባ መድሃኒት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ስለመቻሉ ሣይንሳዊ ማስረጃ የለም፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ