መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 25፣2012-በሊቢያ የሚገኙ ተፋላሚ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ

በሊቢያ የእርስ በርስ ቀዉስ ዉስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸዉ ተፋላሚ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸዉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተልዕኮ አስታዉቋል፡፡በዚህም መሰረት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈዉ የትሪፖሊ መንግስትና የጄነራል ሀፍታር ሀይሎች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሷል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈዉ የትሪፖሊ መንግስት መቀመጫዉን በትሪፖሊ ያደረገ ሀይል ሲሆን የቱርክ መንግስት ዋንኛ ድጋፍ ያገኛል፡፡በጠቅላይ ሚንስትር ፋይዝ አል ሳራጅ የሚመራ ጥምረት ነዉ፡፡ትሪፖሊና ሚስራታ በስሩ ይገኛሉ፡፡

የቶብሩክ አስተዳደር የሚባለዉና በጠንካራዉ የጦር ሰዉ ጄነራል ካሀሊፍ ሀፍታር ሀይሎች የሚመራዉ ጥምረት ቤንጋዚንና በረሃማዉን የሊቢያ ግዛቶችን ያካተተ ስፍራ ነዉ፡፡ሊቢያ ከቀድሞ መሪዋ ሙሃመር ጋዳፊ በኔቶ መራሹ ጥምረት ከስልጣን መወገድ በኃላ መረጋጋት ርቋት ይገኛል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *