መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 25፣2012-በሴኔጋል በርካታ መምህራን በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ የትምህርት ቤቶች በድጋሚ የሚከፈቱበት ቀን ተራዘመ

ለሳምንታት ተዘግተዉ የቆዩ ትምህርት ቤቶች በድጋሚ ለመክፈት ማክሰኞ ቀጠሮ ቢያዘም በቫይረሱ የተያዙ በርካታ መምህራን መገኘታቸዉ ተከትሎ ቀኑ እንዲራዘም ተደርጓል፡፡በሴኔጋል 3,739 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ43 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በሌላ መረጃ በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ150ሺ በልጧል፡፡የ1.3 ቢሊየን ህዝብ መኖሪያ በሆችዉ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ150ሺ መብለጡን የአለም የጤና ድርጅት አስታዉቋል፡፡ትምህርት ቤቶችና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በድጋሚ መከፈት ሲጀምር ስጋቱ እንደሚጨምር መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *