
በቻይና ዉሃን ማዕከላዊ ሆስፒታል ሲሰሩ የነበሩትና ከአራት ወራት በፊት በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ሪፖርት የተደረገዉ ዶክተር ሁ ዊፊንግ ህይወታቸዉ ስለማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፡፡በህክምና ክትትል ላይ ሳሉ ቀይ የፊት ገጽታቸዉ ወደ ጥቁር መቀየሩ አነጋጋሪ ሆኖ የነበረ ሲሆን ባጋጠማቸዉ የጉበት ጤና መታወክ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ከቫይረሱ እያገገሙ እንደነበር ሲገለጽ ቢቆይም ህይወታቸዉ ማለፉን ግሎባል ታይምስ ለንባብ አብቅቷል፡፡ለማጅራት ገትር በሽታ ይሰጥ የነበረዉን ፖሊሚክሲን ቢ መድሃኒት ይወስዱ እንደነበረም ታዉቋል፡፡
ስምኦን ደረጄ