
ጉብኝቱ በትናትናው ዕለት በጋምቤላ ከተማ የተጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ (በፓጋግ) እንደሚቀጥልና በመጨረሻም ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡
ጉብኝት ከተደረገባቸው መካከል በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የህክምናና የለይቶ ማቆያ ቦታ ፣ በጋምቤላ ከተማ የሚገኘው የኮቪድ 19 መመርመሪያ ላብራቶሪ፣ የጋምቤላ ሪፈራል ሆስፒታልና የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ይገኙበታል፡፡
ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የህክምና ተቋማት ያላቸው ዝግጁነት በየጊዜው እየተገመገመ ማሻሻዎች እየተደረጉ ይገኛል።