መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 26፣2012-በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ የማለዳ ወሬዎች

 በዩናይትድ ስቴትስ እየተደረገ ያለውን ተቃውሞ አጋርነት ለማሳየት በሎስ አንጀለስ ከተማ የፖሊስ እና የወታደር አባላት በጉልበታቸው በመንበርከክ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ በተመሳሳይ በጆርጂያና አትላንታም ይኸው ተግባር ተደግሟል፡፡

 አሜሪካዊው ራፐር ጄ ዚ ሙሉ ገፅ ፅሁፍ በተለያዩ ጋዜጦች ሽፋን ያገኘለትን ለጆርጅ ፍሎይድ መታሰቢያ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ መልዕክቱ ከ 1965 የማርቲን ሉተር ኪንግ መልዕክት የተወሰደም ነው፡፡ በኒውዮርክ ታይም ፣ ቺካጎ ትሪቡን ፣ ሎስ አንጀለስ ታይምስ እና ዴንቨር ፖስት ላይ ሽፋን አግኝቷል፡፡

 የጆርጅ ፍሎይድ የ 6 ዓመቷ ልጁ ወላጅ እናት ጊኦና ‹‹ ልጃችን ከዚህ በኋላ አባት የላትም ፤ ስታድግ አትመለከታትም›› ስትል በሚኒያፖሊስ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናገረች፡፡

 በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች እንቅስቃሴን የሚገድብ ህግ መጣሉን ተከትሎ ፤ ዶናልድ ትራምፕ በቲውተር ገፃቸው ዋሽንግተን ዲሲ ትናንትና ምሽት የዓለማችን ሰላማዊ ስፍራ ሁኖ አምሽቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 በዋሽንግተን ዲሲ ፖሊስ መንገድ መዝጋቱን ተከትሎ አንድ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ 80 ሰዎች በማስጠለል ከእስር መታደጉ ተሰማ፡፡ የዋሽንግተን ፖሊስ 200 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *